ቀጣዩ የውድድር ዘመን የማንቸስተር ሲቲ ተቀናቃኝ ሆኖ የሚቀርበው ቡድን ማነው? - BBC News አማርኛ (2024)

ቀጣዩ የውድድር ዘመን የማንቸስተር ሲቲ ተቀናቃኝ ሆኖ የሚቀርበው ቡድን ማነው? - BBC News አማርኛ (1)

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

እነሆ ዓመት በመጣ ቁጥር አንድ ጥያቄ የምንሰነዝርበት ጊዜ ደርሷል። ለመሆኑ ማንቸስተር ሲቲን የሚያስቆም ቡድን ማነው?

ፔፕ ጉዋርዲዮላ የሲቲን ደጃፍ ከረገጡ ዘጠኝ የውድድር ዘመናት አስቆጥረዋል። ከሦስት፣ አራት፣ አምስት ጊዜ ዋንጫውን እንደሚያነሱ ተስፋ የተጣለባቸው መሆንም አላዳገታቸውም።

ካለፉት ሰባት የፕሪሚዬር ሊጉ ዋንጫዎች ስድስቱን አንስተዋል። አራት ተከታታይ ጊዜ በማንሳት የማይፋቅ የሚመስል ታሪክ ጽፈዋል።

የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ሊጀምር የቀሩት ቀናት ጥቂት ናቸው። ለመሆኑ ሲቲን የሚገታው ማነው? የአምናው የዋንጫ ተስፈኛ አርሰናል? ሊቨርፑል? ወይስ ማንቸስተር ዩናይትድ?

አርሰናል

አርሰናሎች ባለፈው የውድድር ዘመን ከሲቲ በሁለት ነጥብ ዝቅ ብለው ሁለተኛው ሆነው ነው ያጠናቀቁት።

ላለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት ሲቲን መርታት ባይችሉም መገዳደር ያልተሳናቸው መድፈኞቹ ከሌሎቹ የሊጉ ክለቦች የተሻለ ግምት ተሰጥቷቸዋል።

አርሰናል በያዝነው የዝውውር መስኮት አንድ ተጫዋች ብቻ ነው ያስፈረመው። እሱም ጣልያናዊው ተከላካይ ሪካርዶ ካላፊዮሪ። በግራ መስመር አሊያም የመሐል ተከላካይ ሆኖ የሚጫወተው ካላፊዮሪ በ42 ሚሊዮን ፓውንድ ነው ከቦሎኛ አርሰናልን የተቀላቀለው።

ባለፈው የውድድር ዘመን በውሰት መጥቶ ዋናውን ግብ ጠባቂ ከመንበሩ ያፈናቀለው ስፔናዊው ዴቪድ ራያ በአርሰናል ቤት የቋሚነት ፊርማ አስቀምጧል።

ላለፉት ሁለት ዓመታት የአርሰናል ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ያሳለፈው የክንፍ መስመር ተጫዋቹ ቡካዮ ሳካ ነው። የአርሰናል ዋነኛ ችግር ጨራሽ አጥቂ ማጣት ይሆን? የመድፈኞቹ ስም ከናፖሊው ቪክተር ኦሲምሄን ጋር እየተያያዘ ይገኛል።

የቢቢሲ ስፖርት ነባር የእግር ኳስ ፀሐፊ የሆነው አሌክስ ሀዌል አርሰናል ሲቲን ከመንበሩ ለማንሳት አቅም እንዳለው ያምናል።

  • ኢትዮጵያ እስካሁን በኦሊምፒክ ያገኘቻቸው ሜዳሊያዎች ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር ሲነጻጸር

  • በአልጄሪያዊቷ ቦክሰኛ የፆታ ውዝግብ የፑቲን እጅ አለበት?

  • የ2024 ፓሪስ ኦሊምፒክ የሜዳሊያ ሠንጠረዥ

ቀጣዩ የውድድር ዘመን የማንቸስተር ሲቲ ተቀናቃኝ ሆኖ የሚቀርበው ቡድን ማነው? - BBC News አማርኛ (2)

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ሊቨርፑል

ሊቨርፑሎች ባለፈው የውድድር ዘመን ከሲቲ በ9 ነጥብ ዝቅ ብለው በሦስተኛ ደረጃ ላይ ነው ያጠናቀቁት።

ሊቨርፑል ያለአሠልጣኝ ዩርገን ክሎፕ የውድድር ዓመቱን ሲጀምር ይህ ከአውሮፓውያኑ 2015 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል።

ክሎፕ ክለቡን ለቀው እንደሚቀጡ ያስታወቁት ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ሲሆን አዲሱ አሠልጣኝ አርን ስሎት ያለፈው ግንቦት መንበራቸውን ተረክበዋል።

ኔዘርላንዳዊው አሠልጣኝ ሊቨርፑል ከሚታወቅበት ተጭኖ የመጫወት አሠለጣጠን ለየት ባለ ኳስን ይዞ በመጫወት ነው የሚታወቁት።

ሲቲ በሰባት የውድድር ዘመናት ስድስት ዋንጫ ሲያፍስ አንዷን የተቋደሰው ሊቨርፑል ነው። ሊቨርፑል በዘንድሮው የውድድር መስኮት ምንም ተጫዋች ባያስፈርምም ስሎት ግን ይህ በቅርቡ ይቀየራል ይላሉ።

የቢቢሲ ስፖርት ነባር የእግር ኳስ ፀሐፊ ኒዛር ኪንሴላ አርን ስሎት ገና ጀማሪ ቢሆኑም፣ ሊቨርፑል ሲቲን የመገዳደር ተስፋ አለው ቢልም ባይሳካላቸው እንኳ አዲስ አሠልጣኝ መቅጠራቸው ከግምት ውስጥ መግባት አለበት ሲል ይከራከራል።

አስተን ቪላ

ቪላ ባለፈው ዓመት አስደናቂ ብቃት በማሳየት አራተኛ ሆኖ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊነቱን አረጋግጧል።

ከሲቲ በ23 ነጥብ ርቆ ያጠናቀቀው አስተን ቪላ በኡናይ ኤምሪ አሠልጣኝነት ዘመን ከሊጉ ከመውረድ ተርፎ የዋንጫው ተፎካካሪ እስከመሆን ደርሶ ነበር።

ቪላን ከያዙ ሁለት ዓመት እንኳ በቅጡ ያልሞላቸው ኡናይ በፕሪሚዬር ሊጉ ሕግ መሠረት የተወሰኑ ተጫዋቾችን የመሸጠ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

ቢሆንም በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾች ማስፈረም ችለዋል። አማዱ ኦናና ከኤቨርተን፣ ኢያን ማትሰን ከቼልሲ፣ ሮስ ባርክሊ ከሉተን እንዲሁም ሁለት ተጫዋቾችን ከአካዳሚ ማስመጣት ችለዋል።

የቢቢሲ ስፖርት ከፍተኛ የስፖርት ዘጋቢ የሆነው ኒክ ማሺተር እንደሚለው ከወራጅ ቀጠና ሦስት ነጥብ ርቀው እያሉ የመጡት ኡናይ ክለቡን ለውጠውታል።

የቪላዎቹ ዳግላስ ሉዊዝ እና ሙሳ ዲያቢ ክለቡን ለቀዋል። ኒክ እንደሚለው ምንም እንኳ ቪላ ከባድ ለውጥ ቢያሳዩም ሲቲን ይገዳደራሉ ለማለት ጊዜው ገና ነው።

ቀጣዩ የውድድር ዘመን የማንቸስተር ሲቲ ተቀናቃኝ ሆኖ የሚቀርበው ቡድን ማነው? - BBC News አማርኛ (3)

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ቶተንሀም ሆትስፐር

ባለፈው የውድድር ዘመን ከሲቲ በ25 ነጥብ ርቀው አምስተኛ ሆነው ነው ያጠናቀቁት።

ቶተንሀም ያለፈውን የውድድር ዘመን በአንጅ ፖስቴኮግሉ አሠልጣኝነት በብሩህ ብቃት ቢጀምርም በስተመጨረሻ ግን ከአንድ እስከ አራት ያለው ቦታን ለቆ ወጥቷል።

ቶተንሀም በዝውውር መስኮት ሦስት ታዳጊ ተጫዋቾችን ከ18 ዓመት በታች ለሆነው ሁለተኛው ክለብ ቢያስፈርምም ልምድ ያለው ተጫዋች እስካሁን አላስመጣም።

እንደ ኒዛር ኪንሴላ ከሆነ አሠልጣኙ አሁንም አሪፍ አጨዋወት ቢያሳዩንም ዋንጫ ባያነሱ እንኳ በቻምፒዮንስ ሊጉ ለመሳተፍ መጫወታቸው አይቀርም።

ቼልሲ

ቼልሲ ያለውን የውድድር ዘመን ከሲቲ በ28 ነጥብ ርቆ ስድስተኛ በመሆን ነው ያጠናቀቀው።

አብዛኛውን ጊዜ የሊግ አጋማሽ ላይ የከረመው ቼልሲ በመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች ነጥብ በመሰብስብ በሚቀጥለው የአውሮፓ ሊግ ዋንጫ እንደሚሳተፍ ማረጋገጥ ችሏል።

ሌስተር ሲቲን ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ ማሳደግ የቻሉት ኤንዞ ማሬስካ የቀድሞውን አሠልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲንሆ ተክተው ተሹመዋል። በርካታ ልምድ ያላቸውን እና የሌላቸውን ተጫዋቾችን አስፈርመዋል።

አንጋፋው ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫን ጨምሮ አራት ተጫዋቾች ክለቡን ሲሰናበቱ ኮነር ጋላገር ደግሞ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ እንደሚያቀና እየተነገረ ነው።

ኪንሴላ የቼልሲ ዒላማ መሆን ያለበት በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ መሳተፍ ሌሎች የአገር ውስጥ ዋንጫዎችን ለማንሳት መታገል ነው ብሎ ያምናል።

ኒውካስል ዩናይትድ

ኒውካስል ባለፈው ዓመት ከሲቲ በ31 ነጥብ ርቀው ሰባተኛ ሆነው ነው ያጠናቀቁት።

ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ደርሰው ብዙዎችን አስገርመው የውድድር ዓመቱን የጀመሩት ኒውካስሎች አጨራረሳቸው ያማረ አልሆነም።

ማንቸስተር ዩናይትድ የኤፍ ኤ ዋንጫውን በማንሳቱ ምክንያቱ ኒውካስል በአውሮፓ ውድድሮች ለመሳተፍ የነበራቸው ሕልም መክኗል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሊሆን ይችላል እየተባለ የሚታማው አሠልጣኝ ኤዲ ሀው ዋና ዋና የሚላቸው ተጫዋቾችን ከቡድኑ ላለመጣት ያደረገው ጥረት የተሳካ ይመስላል።

የቢቢሲ ስፖርት ነባር ጋዜጠኛ የሆነው ሳይመን ስቶን እንደሚለው ኒውካስል በፕሪሚዬር ሊጉ በጣም የተጎዱ ይመስላሉ። በዚህ ሕግ መሠረት ኒውካስል ተጫዋቾችን ሳይሸጥ ሌሎች ተጫዋቾች መግዛት አይችልም።

ቀጣዩ የውድድር ዘመን የማንቸስተር ሲቲ ተቀናቃኝ ሆኖ የሚቀርበው ቡድን ማነው? - BBC News አማርኛ (4)

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ማንቸስተር ዩናይትድ

ቀያዮቹ ሰይጣኖች ያለፈውን የውድድር ዓመት ከሲቲ በ31 ነጥብ ዝቅ ብለው ስምንተኛ ሆነው ነው ያጠናቀቁት።

ከ1989/90 የውድድር ዘመን በኋላ በጣም የከፋ የሚባል የውድድር ጊዜ ያሳለፉት ዩናይትዶች በስተመጨረሻ የኤፍ ኤ ዋንጫን በማንሳት ዘመኑን በድል ጨርሰዋል።

ሥልጣናቸውን ሊያጡ ይችላሉ ተብለው ሲታሙ የነበሩት አሠልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ውላቸውን አራዝመዋል።

የቦሎኛው አጥቂ ጆሽዋ ዚርክዚ በ36.5 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲሁም የሊል የመሐል ተከላካይ የሆነው ሌኒ ዮሮ በ52 ሚሊዮን ፓውንድ ክለቡን ተቀላቅለዋል። ነገር ግን ዮሮ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ለወራት ከሜዳ ሊርቅ ይችላል።

ፈረንሳዊያኑ ራፋኤል ቫራን እና አንተኒ ማርሻል ክለቡን በነፃ ከለቀቁ ተጫዋቾች መካከል ናቸው።

ሳይመን ስቶን አዲሱ ፈራሚ ዮሮ መጎዳቱ ባለፈው የውድድር ዘመን በጉዳት ሲታመስ ለነበረው ዩናይትድ አሳዛኝ ዜና ነው ይላል። አክሎ ዩናይትድ በሚቀጥለው ዓመት ስምንተኛ ሆኖ መጨረሱ ለኤሪክ ቴን አገር የማይዋጥ ትርክት እንደሆነ ይናገራል።

ቀጣዩ የውድድር ዘመን የማንቸስተር ሲቲ ተቀናቃኝ ሆኖ የሚቀርበው ቡድን ማነው? - BBC News አማርኛ (2024)
Top Articles
Latest Posts
Article information

Author: Saturnina Altenwerth DVM

Last Updated:

Views: 6310

Rating: 4.3 / 5 (44 voted)

Reviews: 83% of readers found this page helpful

Author information

Name: Saturnina Altenwerth DVM

Birthday: 1992-08-21

Address: Apt. 237 662 Haag Mills, East Verenaport, MO 57071-5493

Phone: +331850833384

Job: District Real-Estate Architect

Hobby: Skateboarding, Taxidermy, Air sports, Painting, Knife making, Letterboxing, Inline skating

Introduction: My name is Saturnina Altenwerth DVM, I am a witty, perfect, combative, beautiful, determined, fancy, determined person who loves writing and wants to share my knowledge and understanding with you.